Teaching

የዮሐንስ ወንጌል
  • ከብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ሐሳብ ጋር ያለው ግንኙነት
  • በናዜሬት ከተማ ያደገው ኢየሱስ አስቀድሞ በሕግ ፣በነቢያት እና በመዜሙራት ሲነገርለት የነበረው፤
  • ሲጠበቅ የነበረው መሲህ እርሱ ኢየሱስ እንደ ሆነ ለእስራኤላዊያን ለማሳሰብ እንደ ድልድል የሚያገለግል፤
  • ክርስቶስን ለማሳወቅ እንጂ አይሁዳዊነትን ለመተካት የመጣ አዲስ ትምህርት አለመሆኑን ለአይሁድ ሕዜብ ለማሳሰብ የሚረዳ መጽሐፍ ነው፤
  • በመጽሐፉም የተደረጉት ታዓምራቶች ሁሉ ይህንን የሚያመለክቱ “ምልክቶች” ናቸው፡፡

ለምሳሌ፡-  

  • በቃና ገሊላ የመጀመሪያው ምልክት ብሎ ይጀምራል ጸሀፊው፡፡
  • የሳምራዊቷ ሴት ንግግር በራሱ ይህንን አመላካች ነው፡፡ 4፡25
  • ወደ ዮሐንስ መጥመቁ የተላኩት መልዕክተኞች፡፡1፡19-21

ተጨማሪ ያንብቡ

ሰው እና ኃጢአት

በዚህ ኮርስ ውስጥ ሁል ጊዜ በሰዎች ሕይወት ውስጥ የሚነሱ የተለመዱ ጥያቄዎችን ለመመለስ ይረዳል፡፡ በተለይም

  • እኔ ማነ ነኝ ?
  • ከየት መጣሁ ?
  • ለምንድር ነው የምኖረው ?
  • ከሞት በኋላ ምን እሆናለሁ ?

የሚለት ነገሮች ትክክል አሊያም ትክክል ባለሆነ መልኩ በሰዎች አእምሮ ውስጥ ሊቀመጡ ይችላሉ፤ በመሆኑም እነዚህን ጥያቄዎች በተገቢው መንገድ መጽሐፍ ቅዱሳዊ በሆነ መልኩ መመለስ እና ማሳየት የዚህ ኮርስ ዓላማ ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ

ሮሜ እና ገላታይን

ሐዋርያው ጳውሎስ በአገልግሎቱ ለብዘዎች ወንጌልን ሰብኮአል እጅግ በጣም ብዘ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያንን ተክሎአል ፣ ቅዱሳንን አጽናንቶአል አበረታቶአል እንዲሁም ወደ 13 ወይም 14 የሚደርሱ ደብዳቤዎችን ጽፎአል፡፡ ሁሉም መልዕክቶቹ እጅግ በጣም ወሳኝ የሆኑ ሥነ-መለኮታዊ ትምህርቶችን የያዘ ቢሆኑም እነዙህ የድነት ደብዳቤዎቹ ግን እጅግ ጥልቅ የሆኑ ሐሳቦችን ያቀረበበት ነው፡፡

በእርግጥ መጽሐፍ ቅዱስ ይሆናል ብሎ አስቦ ተ዗ጋጅቶ ባይጽፋቸውም በእግዙአብሔር መንፈስ እየተነዳ በመጻፉ ምክንያት መለኮታዊ የሆነ የእግዙአብሔርን ሐሳብ ገላጭ መልዕክቶች ሆነዋል፡፡ በመሆኑም እግዙአብሔር በክርስቶስ ያደረገውን የሰዎችን ልጆች የማዳን ሥራ ትልቅ አፅንዖት ተጥቶታል፡፡ በተለይም ደግሞ አይሁድም ሆኑ አሕዚቦች በአንድ አካል በክርስቶስ ያለ ልዩነት የተስፋውን ቃል ወራሾች መሆን በጳውሎስ ሥነ-መለኮት ውስጥ ትልቅ ትንታኔ የተሰጠበት ነው፡፡ በተጨማሪም አይሁድ ከእግዙአብሔር የማዳን አጀንዳ አንጻር ያላቸው ስፍራ ከየትኛውም የጳውሎስ መልዕክቶች ይልቅ ትልቅ ሽፋን የሰጠበት መልዕክቱ ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ

Christology