Biography

About The Visionary

የባለ ራዕዩ ማንነት ታሪክ ባጭሩ

አንድ መፅሀፍ ሊሆን የሚችልን የህይወትና አገልግሎት ታሪክ በጭምቅ እና ጥቅል ሀሳብ ማስቀመጥ በእርግጥ ቀላል አይሆንም ነገር ግን ብሞክረው እንዲህ ማለት እችል ይሆን?? የሰው ልጆች ሁሉንም የእድሜ ክልል የመኖር እድልበአምላክ ቸርነት ከገጠማቸው ወይ በልጅነት ወይም በወጣትነት ወይም በጎልማሳነት አልያም በእርጅናቸውከፈጣሪያቸው ጋር የመታረቅና እውነተኛውን አምላክ ወደ ማምለክ ይመጣሉ፡፡ እኔም ታዳጊ ወጣት በነበርኩበት ውቅትከዛሬ 33 ዓምት በፊት ክርስቶስን የግል አዳኝ በማደረግ መከተል ጀመርኩ፡፡

ገና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ስለነበርኩና ሀገራችን ኢትዮጵያ የምትከተለው ፖለቲካል አይዲዎሎጂ ኮሚንስት ስለነበረ እና የእምነት ነፃነት ባለመኖሩ ምክንያት እንደ መንግስት አማኞችን ሁሉ የሚያስርበት እና የሚያሰቃይበት ህብርተሰቡ እናወላጆች ልጆቻቸውን የሚያገሉበት ወቅት ስለነበረ እኔም  ልክ እንደማንኛውም አዲስ የክርስቶስ ተከታይ መሆን የነበረበት ነገረ ሁሉ ገጥሞኛል፡፡ ነገረ ግን የውስጥ ጥማቴ ወንጌልን ላልሰሙት ማሰማት በመሆኑ ከራሴ ቤተሠቦች  አንስቶ እስክ ሰፈር ጉዋደኛ ድርስ መስበክ ጀመርኩ፡፡ ይሁን እንጂ ለግዜው  የሚቀበል ባይኖርም ከአንድ ዓመት ቦሃላ ግንበሁለት ቤተሠብ  የጀመረው አሁን አከባቢው በዚህ የወንጌል እውነት በመጥለቅለቁ የተነሳ በየመንደሩና በየቀበሌውእጅግ ብዙ አጥቢያ ህብረቶች ተመስርተዋል፡፡  እኔም  በተወለድኩበት አርሲ መደሮ የመጀመሪያው የሙሉ ግዜ ወንጌላዊ አገልጋይ በመሆን በሶስት የገጠር ከተሞች ማለትም ፤ በመደሮ: በጢቾ እና በኬላ  በመቀመጥ ህብረቶችን ማደራጀትናየዳኑትን አማኞች ደቀመዝሙር ማድረግ ዋና ሰራዬ በማድረግ በብዙ ድካም እንዲሁም ውጣውረድ ግን በበዛው በጌታ ፀጋ አገልግያለሁ::


በዚያም ከአምስት ተከታታይ አመታት አገልግሎት ቆይታ ተተኪ አገልጋዮች በመፍራታቸውና በአንጻሩ በሌላ ከተማ ማለትም አርሲ ሮቤ ዙሪያ አገልጋይ በመጥፋቱ ምክንያት የአሰላ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ባደረገችልኝ ጥሪ መሰረት ወደዚያ መንቀሳቀስ ግድ ሆነብኝ፡፡ ዋና ማዕከሌንም በሮቤ ከተማ በማድረግ በገጠር ትንንሽ ከተሞች እንደ ሰዲቃ፣ በሌ : አዴሌ : ሴሩ: እንዱሁም  ኩላ በመመላለስ ህብረቶችን በማደራጀት ለተከታታይ ለሶስት አመታትእንዳገለገልኩ ለቀጣይ የአገልግሎት ተልዕኮ መዘጋጀት ነበረብኝ፡፡ ከዚህም የተነሳ  በአግዚአብሔር ቃል የማደግ ፍላጎትናበይበልጥም  አማኞች ክርስቶስን ወደመምሰል እንዲያድጉ  ባለኝ ልዩ  ሸክም በአዲስ አበባ ፔንቴኮስታል ቲዮሎጂካል  ኮሌጅ ለሁለት አመት በመከታተል በዲፕሎማ ተመርቄ በቀጥታ የፔንቴኮስታል አሴምብሊ ኦፍ ካናዳ ሚሽን ስር የስነመለኮት በቤቴ መንፈሳዊ የስልጠና ዘርፍ አርሲና ባሌ ሪጅናል ዋና አስተባባሪ በመሆን  አብያተ ክርስቲያንን አገልግያለሁ፡፡

በዚህም ብዙ አገልጋዮች በእግዚአብሐር  ቃል እንዲያድጉ ምክንያት ሆኖአል፡፡ በተጨማሪም  ጎን ለጎን  የአሰላ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያንን በአስተማሪንት እና የወንጌላውያን አገልጋዬች ዋና ተወካይ እና የመሪዎችአባል በመሆን ለሰባት ዓመታት አገልግያለሁ፡፡ በወቅቱም በአብዛኛው በአርሲ ክፍለ ሀገር  ያሉትን የሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን አማኞች አገልጋዮችን በተለያየ ዙር ከማስተማር እና ከማሰልጠን በተጨማሪ በክረምት ወቅት የሁለተኛ ደረጃ የሁሉም ቤተ ዕምነት ክርስቲያን ተማሪዎችን ለሁለት ወር መሰረታዊ የክርስትና ትምህርት ከሌሎች አስተማሪዎች ጋር በመስጠት በዚህም  ትውልድን በማነጽ ታላቅ ሰራ ተሰርቶአል፡፡ በዚህም የአሰላ አብያተ ክርስቲያናት ህብረት የምስጋና የምስክር ወረቀቶችን አበርክቶአል:: ከዚህም ባሻገር በአራቱም ማዕዘናት የኢትዮጵያ ከፍል ከጫፍ እስከ ጫፍበመዘዋወር ልዩ ልዩ ኮንፍራንሶችን በማድረግ እጅግ ብዙ ስዎች ወደ ጌታ መምጣት ምክንያት በመሆን በጌታ ፀጋ አግልግያለሁ::


በ2010 እንደገና ግሎባል ዩኒቭርስቲ ከ አሴምብሊ ኦፍ ጎድ ጋር በመተባብር የሚሰጠውን  የስነመለኮት ትምህርትበሃይማኖታዊ ትምህርት ዲግሪ /BA in Religious Education/ በማግኘት ለተለያዩ አብያተክርስቲያናት ትምህርትናስልጠናዎች  እየሰጠው ቆይቼ  በዛው ዓመት ወደ ጋብቻ ህይወት የገባሁበት ስልሆነ በ 2014 ዓም ወደ ዩናይት ኪንግደም ለንደን ከተማ በመምጣት በዚህም ቀደም ሲል በኢትዮጰያ በጌታ ፀጋ ሳገለገል እነደነበረው በቤተክርስቲያን በተለያዩርዕሶች በለንደን እና ከለንደን ውጭ  ባሉ የዩናይትድ ኪንግደም ዋና ዋና ከተሞቸ በማስተማር ቀጠልኩ።


አሁንም ለእግዚአብሔር ቃል ባለኝ ጥማት እና አብያተክርስቲያናት ክርስቶስን ብቻ ማዕከል ያደረገ አስተምህሮለመስጠት ባለኝ ልዩ ራዕይ የሁለተኛ ድግሪ  ትምህርት ለሁለት  አመት በመከታተል ክርስቲያን ሚኒስትሪ በሮሀምፕተንዩኒቨርስቲ (MA in Christian Ministry in Roehampton University ) አጥንቻለሁ፡፡ በዚህም  በህይወት እንጀራቤተክርስቲያን ያሉትን አማኞች በብዛት የማገልገል ዕድሉ ቢኖረኝም በሁሉም ከፍለ አህጉር ያሉትን  አማኞችእውነተኛውን የክርስትና አስተምህሮ ለማስተማር በማሰብ ይህ የክርስትና ትምህርት አገልግሎትን በመጀመር በአሁኑወቅት የምክር አገልግሎት፤ ልዩ ልዩ መንፈሳዊ ኮርሶችን የመስጠት አገልግሎት፤ እንዲሁም ስብከቶችንና ትምህርቶችን ከተለያዩ ስልጠናዎች  ጋር ለመስጠት የጌታ ፀጋ ባበዛልኝ ልክ ራሴን ያዘጋጀው ሲሆን ዘመኑ ባፈራቸው የመገናኛመስመሮች ሁሉ  ለማገልገል ዝግጁ ነኝ::